



አዲስን ሹክ ይበሉት 😉
አዲስ AI ረዳት መተግበሪያ። በዘመናዊ LLM ቴክኖሎጂ የተገነባ፣ ይህ መተግበሪያ በተለያዩ ስራዎች ላይ ያግዝዎታል።
የጽሁፎን አጋዥ
ታሪኮችን፣ ግጥሞችን እና ድርሰቶችን ይፃፉ፣ መነሻ ሃሳብ ለማመንጨትም ይጠቀሙት
ለ ኮዲንግ
የሚጽፉት ኮድ ላይ እርዳታ ይሻሉ? ሁሉንም የፕሮግራሚንግ ላንጉዊጅ ላይ ያሎትን ጥያቄ ይመልሳል
የጠቅላላ ዕውቅት መረጃ
ላሎት የትኛውም ዕውቅት ላይ የተመሰረተ ጥያቄ አዲስ AI መልስ አያጣም
ለትምህርትዎ
የሚማሩት ትምህርት ላይ እርዳታ ከፈለጉ አዲስን ይጠይቁ ከበቂ ማብራሪያ ጋር ያስረዳዎታል
የመተግበሪያ ባህሪያት
አዲስ AI - የእርስዎ የአማርኛ የAI ጓደኛ!
አዲስ AI: ጓደኛዎ፣ ረዳትዎ፣ ሁሉም በአንድ! በአማርኛ ተፈጥሯዊ ውይይት ያድርጉ። ጥያቄዎን ይጠይቁ፣ መልስዎን ያግኙ። 🎉
AI ረዳት
ይህ በLLM ቴክኖሎጂ የተገነባ ረዳት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተዘጋጀ ነው። ተማሪዎች የጽሑፍ ርዕሶችን ለማሰብ፣ ተመራማሪዎች ጥናትታቸውን ለመደገፍ ኮደሮች ፕሮጀክቶቻቸውን ለማሳለጥ፣ ስራ ፈላጊዎች ማራኪ የስራ ደብዳቤ ለመጻፍ፣ እና የተጠመዱ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ለማደራጀት ይችላሉ። ልክ እንደ የግል ረዳት ነው። ሞክረው እና ህይወትዎን እንዴት እንደሚያቀልል ይመልከቱ።

ተርጓሚ
ረጅም የድምጽ ቅጂዎችን መተርጎም አስቸጋሪ ሆኖብዎታል? አዲስ አጋዥ እስከ አንድ ሰዓት የሚደርሱ የድምጽ ቅጂዎችን በፍጥነት እና በትክክል ወደ ጽሑፍ ይቀይራል። ቃለ መጠይቆችን፣ ንግግሮችን፣ ትምህርቶችን ወይም ሌሎች ረጅም የድምጽ ቅጂዎችን መተርጎም ቢያስፈልግዎት አዲስ አጋዥ ጊዜዎን እና ጉልበትዎን ይቆጥብልዎታል።

ለተማሪዎች
በአንድ የተወሰነ ርዕስ ላይ ጽሑፍ ለመጻፍ ሲቸገሩ፣ AI ረዳት አስደሳች እና አመሳስል ያላቸውን ርዕሶች ሊሰጥዎ ይችላል።
ለሥራ ፈላጊዎች
አስደናቂ የሆነ የሥራ ደብዳቤ ለመጻፍ እና ለቃለ መጠይቅ ለመዘጋጀት የሚረዱዎትን ጥያቄዎች እና መልሶች ሊሰጥዎ ይችላሉ።
ለተመራማሪዎች
የምርምር ወረቀቶችን፣ ጽሑፎችን፣ አጭር መጣጥፎችን እና ሌሎች አካዳሚክ ሰነዶችን ለመጻፍ ጠቃሚ መሣሪያ ነው።
የቋንቋ ችሎታን ለማሻሻል
የእንግሊዘኛ ችሎታዎን ለማሻሻል ይረዳዎታል። ለምሳሌ፣ አንድ አጭር ታሪክ በእንግሊዘኛ ተርጉምልኝ ብለው መጠየቅ ይችላሉ።
አዲስ AI እንዴት ይሰራል?
አዲስ AI በድምፅ መመሪያ የሚሰራ አስደናቂ የAI ረዳት ነው። በቀላሉ ድምጽዎን በመጠቀም ጥያቄዎችን ጠይቀው መልስ ማግኘት ይችላሉ።

ድምጽዎን በመጠቀም ጥያቄዎን ይጠይቁ
አዲስ AI ን ከከፈቱ በኋላ፣ ማይክሮፎኑን ጠቅ ያድርጉ እና ጥያቄዎን በአማርኛ በግልጽ ይናገሩ። ለምሳሌ፣ "ዛሬ የአየር ሁኔታ እንዴት ነው?"፣ "አንድ ቀልድ ንገረኝ" ወይም "የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ አንድ ነገር ንገረኝ" ብለው መጠየቅ ይችላሉ።

አዲስ AI ጥያቄዎን ይተነትናል
አዲስ AI የእርስዎን ድምጽ በጥንቃቄ ይቀዳል እና ምን ማለት እንደፈለጉ ለመረዳት ይሞክራል። በጣም የተራቀቀ የAI ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጥያቄዎን በትክክል ይገነዘባል።

መልሱን ያገኛሉ
አዲስ AI በጽሑፍ እና በድምጽ መልስ ይሰጥዎታል። ለምሳሌ፣ የአየር ሁኔታን በተመለከተ ጥያቄ ካቀረቡ፣ ዛሬውኑ የአየር ሁኔታ እንዴት እንደሆነ ይነግርዎታል። ወይም አንድ ቀልድ ከጠየቁ፣ አስቂኝ ቀልድ ይነግርዎታል።
ተጠቃሚዎቻችን ስለኛ ምን ይላሉ

Great Amharic Ai assistant but if you want to stop the read out by the Ai there is no way to do that , also if you add reading option and make the UI better it would be great app to use

I highly recommend this Amharic chatbot! It’s user-friendly, offers accurate responses, and provides rich cultural insights. Perfect for anyone looking to learn Amharic or explore Ethiopian culture. Give it a try!

It was an incredible experience. I am certain that it will significantly enhance the adoption of AI within our local culture. Well done!

በጣም ልዩ ነው በጣም አሪፍ ነው